Ambo University

Learnig for change

 
Notice

 

ማስታወቂያ

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ የ2011 ዓ.ም ምዝገባ የሚካሄደው ጥቅምት 5 እና 6 መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ እንዲሁም በ2011ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር በአምቦዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ የ2011ዓ.ም ምዝገባ ጥቅምት 7 እና 8 2011 ዓ.ምመሆኑን አውቃችሁ 8 ጉርድፎቶግራፍ፣ ሁሉም የትምሀርት ማስረጃዎችን ብርድልብስና አንሶላ ይዛችሁ እንድትገኙ እያሳወቅን፤ በግብርናና እንስሳት ጤናሳይንስ መስክ (ባንድ) የተመደባችሁ በጉደርካምፓስ፣ በቴክኖሎጂተቋም የተመደባችሁ በአዋሮካምፓስ፣ እንዲሁም በሌሎች መስኮች የተመደባችሁ በአምቦዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳወቅን ከምዝገባው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ  በ011-236-2215 መደወል ይችላሉ፡፡

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራር

 

 

 
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞችና መምህራን
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞችና መምህራን ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች በ18/01/2010ዓ/ም በዩኒቨርሲቲዉ ዋና አዳራሽ በተዘጋጀ ፕሮግራም የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታ ሰጡ፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ሰለሞን ማሾ ለተፈናቃዮቹ ባደረጉት ንግግር ምንም እንኳን ለዘመናት ከኖራችሁበት ቀዬ በመፈናቀላችሁ ብታዝኑም የሚራራላችሁና በፍቅር የሚቀበላችሁ ህዝብ ስላላችሁ ልትደሰቱና በእጅጉ ልትጽናኑ ይገባል ብለዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የተገኙ የመንግስት ባለስልጣናትም ተፈናቃዮቹን አጽናንተዉ ወደፊትም ራሳቸዉን ችለዉ እስኪቋቋሙ ድረስ የመንግስትና የህዝቡ ድጋፍ እንደማይለያቸዉ ገልጸዋል፡፡
በእለቱ በዋናዉ የዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ለተገኙት አልባሳትና የምግብ ቁሳቁሶች የተሰጠ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ጀልዱ አካባቢ ለሰፈሩትም እርዳታዉ እንደሚደርስ የእርዳታ አሰባበሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ መምህር ቦንሳ ቶላ ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ ሰራተኞችና መምህራን ከመስከረም ወር ጀምሮ ተቆርጦ የሚሰጥ 30% እና ከዚያ በላይ ደሞዛቸዉን በፍቃዳቸዉ በመስጠት ወደፊትም ከጎናቸዉ እንደማይለዩ ቃል ገብተዋል፡፡
ችግሩ የደረሰባቸዉ ወገኖችም በተደረገላቸዉ አቀባበልና ድጋፍ መደሰታቸዉን ገልጸዉ የዩኒቨርሲቲዉን ማህበረሰብና እጁን የዘረጋላቸዉን ሁሉ አመስግነዋል፡፡
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞችና መምህራን ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች በ18/01/2010ዓ/ም በዩኒቨርሲቲዉ
ዋና አዳራሽ በተዘጋጀ ፕሮግራም የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታ ሰጡ፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ሰለሞን ማሾ ለተፈናቃዮቹ ባደረጉት ንግግር ምንም እንኳን ለዘመናት ከኖራችሁበት ቀዬ በመፈናቀላችሁ ብታዝኑም የሚራራላችሁና በፍቅር የሚቀበላችሁ ህዝብ ስላላችሁ ልትደሰቱና በእጅጉ ልትጽናኑ ይገባል ብለዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የተገኙ የመንግስት ባለስልጣናትም ተፈናቃዮቹን አጽናንተዉ ወደፊትም ራሳቸዉን ችለዉ እስኪቋቋሙ ድረስ የመንግስትና የህዝቡ ድጋፍ እንደማይለያቸዉ ገልጸዋል፡፡
በእለቱ በዋናዉ የዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ለተገኙት አልባሳትና የምግብ ቁሳቁሶች የተሰጠ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ጀልዱ አካባቢ ለሰፈሩትም እርዳታዉ እንደሚደርስ የእርዳታ አሰባበሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ መምህር ቦንሳ ቶላ ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ ሰራተኞችና መምህራን ከመስከረም ወር ጀምሮ ተቆርጦ የሚሰጥ 30% እና ከዚያ በላይ ደሞዛቸዉን በፍቃዳቸዉ በመስጠት ወደፊትም ከጎናቸዉ እንደማይለዩ ቃል ገብተዋል፡፡
ችግሩ የደረሰባቸዉ ወገኖችም በተደረገላቸዉ አቀባበልና ድጋፍ መደሰታቸዉን ገልጸዉ የዩኒቨርሲቲዉን ማህበረሰብና እጁን የዘረጋላቸዉን ሁሉ አመስግነዋል፡፡
 
26ኛዉ የግንቦት 20 የድል በዓል በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በድምቀት ተከበረ…

26ኛዉ የግንቦት 20 የድል በዓል በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በድምቀት ተከበረ…

GINBOT20GINBOT21

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የግንቦት 20 የድል በዓልን 26ኛ ዓመት በዩኒቨርሲቲዉ አዳራሽ የህዝቦች እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ፌዴራላዊ ስርዓት እየገነባች ያለች ሀገር-ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል ግንቦት 19/2009 በድምቀት አክብሯል፡፡

 

የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ታደሰ ቀነአ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር በማንኛዉም ሀገርና ህዝብ ታሪክ አንዱ ገዢ ሌላዉ ተገዢ፣ አንዱ ጨቋኝ ሌላዉ ተጨቋኝ እንድሁም አንዱ ወሳኝ ሌላኛዉ የባይተዋር ተመልካች ሆኖ የጋራ ሀገርን መገንባትና ብልጽግናን ማለም ያልተቻለ ለመሆኑ ታሪክ ምስክር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

ፕሬዚደንቱ አክለዉም የራሳችንን ሀገር እንኳን ያየን እንደሆነ ከአጼዎቹ እስከ ደርግ ዘመነ-መንግስት የነበሩት ስርዓቶች ለሕዝቦች ማንነትና ፍላጎት ቦታ የሚሰጡ ሳይሆኑ ሁሉ ነገር በገዢዎች በጎ ፍቃድ የሚወሰንበት ሀገር ነበረ፡፡ በተለይም በአጼ ሃይለስላሴ ዘመን በኢትዮጵያዉያን ላይ ይደርስ የነበረዉን ጭቆና መሸከም ያቃታቸዉ ሕዝቦች ከተማሪዎች እንቅስቃሴ እስከ አርሶ አደሮች አመጽ በታጀበ አብዮት በ1966ዓ/ም የአጼዉ ስርዓት ተወግዶ እንደ መሬት ለአራሹ ያሉ ለዉጦች ቢመጡም የደርግ መንግስት ይከተለዉ ከነበረዉ እጅግ አምባገነናዊ ስርዓት የተነሳ የሕዝቦችን  ማንነትና ፍላጎት መሰረት ያደረ ዲሞክራሲያዊና ሕዝባዊ መንግስት ማቋቋም ሳይቻል ቀርቷል ብለዋል፡፡

 

ፕሬዚደንቱ እንዳሉት ያ መንግስት ከሕዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን በጉልበት እያፈነ በመሄዱ የሕዝቡን ጥያቄ በትጥቅ ትግል ለመመለስ የሚንቀሳቀሱ የሕዝብ ድርጅቶች ተፈጥረዉ ባደረጉት የጦር ሜዳ ፍልሚያ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ/ም የስርዓቱ መጨረሻ የሆነዉ ድል በመገኘቱ የሕዝቦችን ማንነትና የጋራ ፍላጎት መሰረት ያደረገ ህገ-መንግስት ጸድቆ ስራ ላይ ዉሏል፡፡ በንግግራቸዉ መጨረሻም የግንቦት 20ን የሕዝብ በዓል ስናከብር የትኛዉንም ዓይነት ጭቆና እና ብልሹ አሰራሮችን በመጸየፍ ለራሳችንና ለሕዝባችን ቃላችንን ማደስ አለብን ብለዉ ሁላችንም ባለንበት የስራ ሃላፊነትና ደረጃ በህገ-መንግስታችን መርሆዎች መሰረት ዲሞክራሲያዊነት እና ሕዝባዊነትን እንንከባከብ ሲሉ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

GINBOT22GINBOT23

አቶ መኩሪያ ገ/ማሪያም የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚደንት የኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት ባህሪያት፣ የዲሞክርሲያዊ አንድነት ግንባታ ሂደትና ስኬቶቹ በሚል ርእስ የፓናል ዉይይት መነሻ ጽሁፍ አቅርበዉ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡

GINBOT24

በበዓሉ ላይ የግንቦት 20ን የድል ፍሬዎች የሚያወድሱ ግጥሞችና የብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የአልባሳት ትእይንት ቀርበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ግንኙነትና አሉሚኒ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት

 
Two days’ National Conference Conducted at Ambo University….

Two days’ National Conference Conducted at Ambo University….

Ambo University has conducted the 5th National Research Conference on the theme “Research for Transformation and Sustainable Development” from 9-10 May 2017 at main campus.

nammUntitl20

Dr.Bizunesh Mideksa on the well come speech

Dr.Bizunesh Mideksa, Vice President for Research and Community Service of the University, in her well come speech said that academic and research institutions are highly responsible to carry out problem solving researches to create platforms, to communicate, publish and disseminate their findings so as to address the multifaceted problems and challenges of development in the country. She added that Ambo University has been working diligently to solve social problems through undertaking specific research and rendering community services. As a result of this, said Dr. Bizunesh, the university is dedicated to establish viable research culture that would back up academic staff’s participation and contribution in the research area.

presidentviseP

His Excellency Tadesse Kenea on the opening speech

His Excellency Tadesse Kenea, President of the University said in his opening speech that the day’s occasion was very important platform for stakeholders in research initiatives, both at the institutional and national level, to highlight, discuss and support the emerging research themes and findings and its impact in developing countries like Ethiopia. The president pointed out that there is no country in the world that has no social problems like extremism, racism, corruption, lack of democracy and good governance and so on; and such challenges could be alleviated through big, coordinated, collaborative, coherent, cross-sectorial and trans-disciplinary research initiatives. The president finally underlined that Ambo University management will have devoted support for research undertakings in the future.

Prof. Alemtsehay Mekonnen and Dr. Bekele Gutema from Addis Ababa University have presented papers on titles Enabling and Strengthening Women’s Engagement in Science for Sustainable Development and Research, the Production of Knowledge and Ethical Responsibilities of Universities. Dr. Amsalu Ayana came up with a paper titled Agricultural Education, Research and Extension in Economic Development: National and International Experiences. Totally 63 (40 external & 23 internal) papers were expected and 57 of them were presented, the remaining 5 from external were absent. There was warm discussions and idea sharing among the participants. All the presenters were given certificates at the end of the conference.

GROUPGROUP2

Group photos of the participants

 
ሚያዚያ 19/2009

ለዩኒቨርሲቲዉ የአስተዳደር ሰራተኞች በአዲሱ መዋቅር ድልደላ መመሪያ ላይ  ሚያዚያ 19/2009 አጭር ገለጻ ተሰጠ…

 

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ዓመት አድስ መዋቅር ሰርቶ ማስፈቀዱ ይታወቃል፡፡ በዚህ አዲስ መዋቅር ሰራተኞች በሚደለደሉበት ደንብ ላይ ገለጻ ያደረጉት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ታደሰ ቀነአ የዩኒቨርሲቲዉን ሰራተኞች “እንኳን ድስ አላችሁ!” ካሉ በኋላ የአዲሱን መዋቅር አደላደል ከደንቦችና መመሪያዎች ጋር በማጣቀስ ለሰራተኛዉ ግልጽ አድርገዋል፡፡ ከሰራተኛዉም ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የተሰጠ ሲሆን ፐሬዚደንቱ ድልድሉ ህግንና ደንብን ተከትሎ የሚደረግ ስለሆነ የማንንም መብት እንደማይጋፋ ገልጸዉ ሁሉም ነገር በጥንቃቄ እንደሚሰራና ቅሬታዎችም ካሉ በሚመለከተዉ አካል እንደሚታዩ አስታዉቀዋል፡፡ ድልደላዉም ከዳይሬክተሮች ጀምሮ እስከ መጨረሻ ድረስ በየደረጃዉ ይከናወናል ብለዋል፡፡

 
<< Start < Prev 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 Next > End >>

Page 1 of 10

Calendar

November 2018 December 2018
Su Mo Tu We Th Fr Sa
1 2 3
4 5 6 7 8 9 10
11 12 13 14 15 16 17
18 19 20 21 22 23 24
25 26 27 28 29 30

AU in Photo